Fana: At a Speed of Life!

ፈዋሽነቱ 90 በመቶ የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሁለት ኩባንያዎች ይፋ የተደረገው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት 90 በመቶ ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ከመያዝ ታድጓል ተብሏል፡፡

ክትባቱን ይፋ ያደረጉት የአሜሪካው ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮንቴክ ሲሆን ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ አበርክቶ ነው ብለዋል፡፡

ኩባንያዎች ክትባቱን በስድስት የተለያዩ ሃገራት በ43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሃገራቱ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቱርክ መሆናቸው ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

በሙከራውም በሰዎች ላይ እስካሁን አሳሳቢ የጤና ችግር ያለመታየቱን ነው ባለሙያዎቹ ያነሱት፡፡

ኩባንያዎቹ ክትባቱን በህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን የአሁኑ ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካው ኩባንያ 50 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ እንደሚያቀርብ የገለፀ ሲሆን በ2021 ደግሞ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን እንደሚያመርት ነው ይፋ ያደረገው፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.