Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በ18 ወራት ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀውን የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የፌዴራል ፖሊስ ኪሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ የአልሙኒየም ፎርምወርክ የግንባታ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደርን ጎብኝተዋል።

የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር፥ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ማጠናቀቅ የቻለና በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ታሪክ ያስመዘገበ ግዙፍ መንደር መሆኑ ተገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ ውጤታማ የግንባታ ቴክኖሎጂ ትግበራ ተሞክሮን በማስፋት የመኖሪያ ቤትን ለማቅረብ የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ገልጸዋል።

በመኖሪያ መንደሩ ጥቅም ላይ ስለዋለው የግንባታ ቴክኖሎጂና ተቋሙ በአራት ዓመታት ውስጥ ያስመዘበውን ውጤትም አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ በርከታ ተቋሙ ውስብስብ ችግር ውስጥ የነበረ እና ተቋማወዊ ኅልውናው አደጋ ውስጥ የወደቀ እንደነበር ተናግረዋል።

በአራት ዓመታት ውስጥ ውጤት ማስመዝገቡ ከዚህ በፊት የገጠመው የአመራር ችግር እንደነበር ማሳያ እንደሆነ ተመላክቷል።

በተለይ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ግዙፍ መኖሪያ መንደር ገንብቶ ማጠናቀቅ መቻል በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ አዲስ ታሪክና እና ከፍታ ነው ማለታቸውንም ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።።

የኮርፖሬሽኑ አመራር አሁን ባገኘው ልምድ ሳይዘነጋ የኑሮ ውድነት አንዱ መፍቻ መንገድ የሆነውን የመኖሪያ ቤት እቅርቦት ችግር ለማቃለል ጠንክሮ እንዲሠራ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ማሳሰባቸው ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.