Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ የክለቦች ውድድር ኢትዮጵያን ይወክላሉ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 13፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ረፋድ በተደረገው ጨዋታ የፋሲልን የማሸነፊያ ጎሎች ሙጂብ ቃሲም ከዕረፍት መልስ አስቆጥሯል፡፡

አጼዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 55 ያደረሱ ሲሆን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት በማጥበብ በዋንጫ ፉክክሩ መቆየት ችለዋል፡፡

ፋሲል ከነማ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ በ2022/23 የካፍ የክለቦች ውድድር ኢትዮጵያን መወከሉን አረጋግጧል።

በፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን የሚሆነው ቡድን በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክል ሲሆን ሁለተኛ ሆኖ የሚያጠናቀው ቡድን ደግሞ በካፍ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.