Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ ከሰበታ ከተማ ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማና ሰበታ ከተማ አንድ አቻ ተለያዩ፡፡

ለፋሲል ከነማ ሽመክት ጉግሳ በአምስተኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ቡልቻ ሱራ ለሰበታ ከተማ በ77 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ረፋድ ቀደም ብሎ በተካሄደው ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ጅማ አባ ጅፋርን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ፋሲል ከነማ በ12 ጨዋታዎች 29 ነጥብ በመያዝ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ እኩል 24 ነጥብ ይዘው በግብ ክፍያ በመበላለጥ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ይከተላሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.