Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ሁለቱ ተቋማት በተፈራረሙት ስምምነት መሰረት በአቅም ግንባታና በእውቀት ሽግግር ላይ መስራት የሚችሉ ሲሆን÷ የኮሙኒኬሽን ስራዎችንም እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ስምምነቱ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግም ያስችላቸዋል ተብሏል።

የተፈረመው ስምምነት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ መካከል ጥሩ አቅም ይፈጥራል ያሉት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአስተዳደርና ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሬድዋን ሱልጣን÷ የፋና ስልጠና ማዕከልን የጥራት ማዕከል ለማድረግ በምንሰራበት ወቅት መሆኑ አበረታች ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የከተማውን የልማት ፖሊሲ ታሳቢ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የገለፁት የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ደሳለኝ ጴጥሮስ በበኩላቸዉ÷ ከፋና ጋር በትብብር መስራታችን በሂደት የተሻለ ተቋም ለመገንባት ያስችለናል ነው ያሉት።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የፋና ብሮድካስቲንግ የስርጭት ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.