Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 100 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ በደሴ ከተማ ያስገነባው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ነገ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 100 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ በደሴ ከተማ ያስገነባው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ነገ ይመረቃል።

በ450 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንፃው ባለ 8 ወለል ሲሆን፥ ወቅቱ የደረሰበትን የሬዲዮ ስቱዲዮን ያካተተ ነው።

እንደዚሁም በቀጣይ ተቋሙ ሊኖረው የሚችልን የቴሌቪዥን ስቱዲዮን ታሳቢ አድርጎም እንደተገነባ ተመልክቷል።

በተጨማሪም የስብሰባ አዳራሽ እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎችንም የያዘ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የኤፍ ኤም ጣቢያዎችን በመክፈት የየአካባቢዎቹን ነዋሪዎች በመድረስ ላይ ይገኛል።

በ12 ዓመት የምስረታ በዓሉ ዋዜማ ላይ የሚገኘው ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 0 በከተማዋ እና በዙሪያዋ በሚገኙ የአማራ እና አፋር ክልሎች አካባቢዎች ነዋሪዎችን በማገልገል ላይ ይገኛል።

የዚህ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃትም የይዘት ተደራሽነቱን በጥራት እና በብዛት ለማሳደግ እንደሚያግዝ ታምኖበታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.