Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ነገ ያካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰጠኝ እንግዳው እንደተናገሩት የተቋሙ 25ኛ ዓመት አከባበር አካል የሆነው የፓናል ውይይት የተቋሙን ጉዞና አበርክቶ በመዳሰስ ባለፉት ጥንካሬዎች መነሻነት ተቋሙን የተሻለ ተወዳዳሪ ማድረግና ሀገራዊ ተልዕኮውን እንዲወጣ ማገዝን ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ “ፋና ከየት ወዴት” እንዲሁም “በብሄረ መንግስትና ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚዲያ ሚና” በሚሉ ርዕሶች ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም አቶ ሰጠኝ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ በሀገረ መንግስትና ብሄረ መንግስት ግንባታ ሂደት የሚዲያውን ጠንካራና ደካማ ጎን በመገምገም በቀጣይ ግብዓት የሚሆን ሃሳቦች እንደሚነሱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የመገናኛ ብዙኀንም ራሳቸውን ተመልክተው በቀጣይ ሚናቸውን በመቃኘት አቅጣጫቸውን ለመተለም የሚረዳ ግብዓት ያገኙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው አቶ ሰጠኝ የተናገሩት፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሚዲያ ተቋማት ሃላፊዎች፣ ወጣቶች የሙያ ማህበራት ተወካዮችና ሌሎችም እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

25ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፡ በቀጣይም በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚዲያ ሚና እና በሰላም ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮረ ተመሳሳይ የፓናል ውይይት እንደሚያዘጋጅ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.