Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን በክልል ጣቢያዎች እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን በክልል ጣቢያዎች በማክበር ላይ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬቱ ባለፉት 25 ዓመታት የሰጠውን የሚዲያ አግልግሎት፣ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች እና በቀጣይ ራዕይ ላይ በማተኮር በዓሉን ከደንበኞቹ ጋር እያከበረ ነው፡፡

በዓሉ በዛሬው ዕለት በጅማ፣ ሻሸመኔ፣ ሐረማያና በደሴ ሲከበር፤ ነገ በደብረ ብርሃን በተመሳሳይ ይከበራል፡፡

ፋና ከየት ወዴት የሚል ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፣ በቀጣይ ጥንካሬውን ከፍ በማድረግ፣ ክፍተቶቹን አርሞ በተሻለ የሚዲያ አግልግሎት ለማምጣት ከመድረኮቹ ግብዓት ይሰበሰባል ተብሏል፡፡

በዓሉ አድማጮቹን፣ ደንበኞቹን እና ሰራተኞቹንም የሚያመሰግንበት መድረክም ጭምር ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.