Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ ተጠያቂነት የሚያሰፍን አሰረራር ዘረጋ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ ተጠያቂነት የሚያሰፍን አሰረራር ዘረጋ።

ፌስቡክ ኢትዮጵያና ኬንያን ጨምሮ የማህበራዊ ጉዳይ፣ ምርጫ እና ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ  ተጠያቂነት እና ቁጥጥርን የሚያሳድግ አሰራር እንደሚዘረጋ ነው ያስታወቀው።

በዚህም በኢትዮጵያ በፌስቡክ ማህበራዊ ጉዳይ፣ ምርጫ እና ፖለቲካን በተመለከተ የሚያስተዋውቁ አካላት ፈቃድ መውሰድ እና በፌስቡክ ለሚተላለፉ ይዘቶች ሃላፊነት እንደሚወስዱ ኩባንያው አስታውቋል።

ይህም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገፆቻቸው የሚተላለፉ ማስታወቂያዎችን የበለጠ ቁጥጥር እንዲኖራቸው የሚያስችላቸው መሆኑ ተነግሯል።

በዚህም ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ፣ ምርጫ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ የተወሰነ ማስታወቂያ ብቻ እንዲመለከቱ ያስችላል።

እንዲሁም ተጠቃሚዎቹ የእራሳቸው ፍላጎት እና ሀሳብ በመለየት የማህበራዊ ፣ ምርጫ እና ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር ያስችላቸዋል ነው የተባለው።

ይህም ከመጭው ሀሙስ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ እና በሀገራቱ ከሚካሄዱ ምርጫዎች ጋር እንደሚያያዝም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.