Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ በገጹ ከሚለቀቁ ዜናዎች ጋር በተያያዘ አውስትራሊያ ለሚገኝ አንድ ሚዲያ ክፍያ ለመፈጸም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ በገጹ ከሚለቀቁ ዜናዎች ጋር በተያያዘ በሩፐርት መርዶክ ባለቤትነት ለተያዘው ኒውስ ኮርፕ አውስትራሊያ ክፍያ ለመፈጸም ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡

የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ከሚለቀቁ ዜናዎች ጋር በተያያዘ አውስትራሊያ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ህግ ባለፈው ሳምንት አውጥታለች፡፡

በዚህም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ በገጾቻቸው ላይ ለሚወጡ ዜናዎች ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስገድድ ነው፡፡

የአውስትራሊያ መንግስት ህጉን ሊያወጣ የቻለው አሳታሚዎች ከቴክኖሎጂ መምጣት ጋር ተያይዞ የማስታወቂያ ገቢ በማጣታቸው ነው ተብሏል፡፡

የፌስቡክ ኩባንያ በአሁኑ ስምምነት ገጹ ላይ ለሚወጡ ዜናዎች ክፍያ ለመፈጸም ነው የተስማማው፡፡

የኒውስ ኮርፕ ሃላፊ ሮበርት ቶምሰን ስምምነቱ ታሪካዊ ብለውታል፡፡

ኒውስ ኮርፕ አውስትራሊያ በስሩ የተለያዩ ጋዜጦችን የሚያስተዳድር ሲሆን የሀገሪቱን 70 በመቶ የገበያ ስርጭት እንደሚቆጣጠርም የቢቢሲ መረጃ ያሳያል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.