Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ የትራምፕ ደጋፊዎችን ቡድን አገደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌስቡክ ኩባንያ የትራምፕ ደጋፊዎችን ቡድን ማገዱን አስታወቀ፡፡

ይህ በትራምፕ ደጋፊዎች የተከፈተውን “ስቶፕ ዘ ስቲል” የተሰኘው ቡድን በአንድ ቀን ብቻ 350 ሺህ ሰዎች ወደ አባልነት ተቀላቅለው እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡

ቡድኑ የተቋቋመው ድምጻችን እየተሰረቀ ነው በሚሉ የትራምፕ ደጋፊዎች ነው፡፡

ይህን ተከትሎም የፌስቡክ ኩባንያ ግጭት ሊቀሰቅስ ይችላል በሚል አግዶታል፡፡

የኩባንያው ቃልአቀባይ የቡድኑ ድርጊት የምርጫ ሂደቱን ህጋዊነት ለማሳጣት ያለመ ነው ብለውታል፡፡

በአንጻሩ የቡድኑ አስተዳዳሪዎች ግራ ዘመሞች ድምጽ ለመስረቅ እየሞከሩ ነው በማለት ትዊተር ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

የኩባንያው ድርጊትም ህግን ያልተከተለ ነው በማለት ተችተዋል፡፡

በአሪዞና የሚገኙ ሰልፍ የወጡ የትራምፕ ደጋፊዎች መታጠቃቸውም ተሰምቷል፡፡

ይህ ጉዳይ ያሳሰበው አምነስቲ ኢንተርናሽናልም ቆጠራ በሚካሄድባቸው ጣቢያዎች የጦር መሳሪያ መታጠቅ እንዲታገድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በፕሬዚዳንት ትራምፕና በዴሞክራቱ እጩ ጆ ባይደን መካከል የሚደረገው የኋይትሐውስ ጉዞ ዛሬ ውጤቱ እንደሚታወቅ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.