Fana: At a Speed of Life!

ፌስቡክ ፣ጎግል እና አማዞን ለአውሮፓና ለታዳጊ ሀገራት 100 ቢሊየን ዶላር ተጨማሪ የኮርፖሬት ግብር ሊከፍሉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ግዙፎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለአውሮፓ እና ለታዳጊ ሀገራት ተጨማሪ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ረቀቅ የግብር ህግ በአውሮፓ ሀገራት መዘጋጀቱ ተገለፀ።

ይህ እርምጃ ከኮርፖሬት ታክስ ጋር ተያይዞ ከፍ ያለ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የየሃገራት ግብር ሰብሳቢዎችም እስከ 4 በመቶ የሚደርስ ተጨማሪ ግብር እንዲሰበስቡ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከእነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት እስከ 100 ቢሊየን ዶላር ተጨማሪ ግብር መሰብሰብ እንደሚቻል ነው የተነገረው።

ከተጠቀሱት ተቋማት ባሻገር ቅንጡ ምርት አምራች የሆኑ የአውሮፓ ኩባንያዎች ከሚያገኙት ትርፍ የኮርፖሬት ታክስ እንዲከፍሉ እና ዝቅተኛ ታክስ ወደ ሚከፈልባቸው ሀገራት ማዘዋወር እንደማይችሉ ኒውስዊክ አስነብቧል።

የፖለቲካ ስምምነት ላይ በቀጣዩ ዓመት ከተደረሰ ይህ አዲስ ስርዓት ተፈፃሚ ለመሆን ዝግጁ ነው ሲል የአውሮፓውያኑ የኢኮኖሚክ ትብብር እና የልማት ድርጅት አስታውቋል።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከአውሮፓ ሀገራት ጋር የነበራትን ውይይት በጊዜያዊነት ያቋረጠቸው አሜሪካ ዓለም አቀፉን የዲጂታል ግብር እቅድ በማጣጣል የአውሮፓ ሀገራት በዲጂታል እቅዳቸው ላይ ከቀጠሉ ተጨማሪ ቀረጥ እጥላለሁ ስትል አስጠንቅቃ ነበር።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.