Fana: At a Speed of Life!

ፌዴሬሽኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ላለፉት ዋልያዎቹ 6 ሚሊየን ብር ሽልማት ለማበርከት ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ከ8 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለለተመለሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ዋልያዎቹ) አባላት የ6 ሚሊየን ብር ሽልማት እንዲሰጣቸው ውሳኔ አሳለፈ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎች ማስተላለፉን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም ለዋልያዎቹ የተበረከተው ሽልማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያዉን በሚያደርግበት ሐዋሳ ከተማ እንዲሆን ወስኗል።

በተመሳሳይ ለክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ ለሚሰሩት ስራ ለእያንዳንዱ የክልል እና የከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች 300 ሺህ ብር ድጋፍ እንዲሰጥ እና ስራው በአግባቡ ስለመሰራቱ እያንዳንዱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክትትል እንዲያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.