Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ ባለቤቱን በአሰቃቂ መንገድ የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ እንዲቀጣ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የገዛ ባለቤቱን በአሰቃቂ መንገድ የገደለው ግለሰብ በሞት ፍርድ እንዲቀጣ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
 
በዞኑ ሽርካ ወረዳ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ ሰኢድ ሱልጢ ፈቶ፥ ባለቤቱን 11 ሺህ ብር ወስደሻል በሚል ግጭት ውስጥ መግባቱን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
 
ግጭቱ ተባብሶም የግል ተበዳይ ወይዘሮ ረኢሳ ሃጂ ኢሳ ቤቷን በመልቀቅ ወደ ቤተሰቦቿ መሄዷም በክስ መዝገቡ ላይ ተመላክታል፡፡
 
ይሁን እንጂ ተከሳሽ ቤተሰቦቿ ቤት ድረስ በመሄድ አደጋ ያደረሰባት መሆኑ ነው ነው የተገለጸው፡፡
 
በዚህም ህዳር 11 ቀን 2014 ከቀኑ 12:30 ላይ ለስግደት በገባችበት መስጊድ ተከትሎ በማቅናት በገጀራ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የክስ መዝገቡ ገልጿል፡፡
 
ተከሳሽ ከድርጊቱ በኋላ ለመሰወር ቢሞክርም በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ክትልል በቁጥጥር ስር ውሎ ለፍርድ ቀርቧል፡፡
 
ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ቃል ወንጀሉን መፈፀሙን በማመኑ እና በምስክርና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱም በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 539/1 መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፏል፡፡
 
ጥር 5 ቀን 2014 የተሰየመው ፍርድ ቤቱ ወንጀሉን በገዛ ሚስቱ፣ በሃይማኖት ስፍራና አሰቃቂ በሆነ መንገድ መፈፀሙን በመግለፅ ሌሎችን ያስተምራል በሚል ሰኢድ ሱልጢ ፈቶ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
 
በኢትዮጵያ በፍርድ ቤቶች የተላለፈ የሞት ፍርዱ ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ከተፈረመ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፡፡
 
 
በዮናታን ብርሃኑ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.