Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ አሜሪካ ዊቻት ከኢንተርኔት ላይ እንዳይወርድ የምታደርገውን ሙከራ አገደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአሜሪካ ፍርድ ቤት ዊቻት የተባለው መተግበሪያ ከኢንተርኔት ላይ እንዳይወርድ (ዳውንሎድ እንዳይደረግ) የምታደርገውን ጥረት ማገዱ ተሰማ፡፡

ሃገሪቱ ባሳለፍነው ሳምንት  ዊቻት እና የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነው ቲክቶክ መተግበሪያዎች ከኢንተርኔት ላይ እንዳይወርዱ እገዳ መጣሏ ይታወሰል፡፡

እገዳውም ከትላንት ጀምሮ ነበር ተግባራዊ የሚደረገው፡፡

ነገር ግን አሁን የአሜሪካ ፍርድ ቤት ሃገሪቱ የቻይና መተግበሪያ የሆነውን ዊቻት ከኢንተርኔት ላይ እንዳይወርድ  የምታደርገውን ሙከራ ማገዱ እየተነገረ ነው፡፡

በዚህም የአሜሪካው  ዳኛ ሎሬል ቢለር እገዳው ህገ መንግስቱ ላይ የተደነገገውን የመናገር ነፃነት ዋስትና የሚፃረር እና ከዋስትና ጋር  የተዛመዱ ጥያቄዎች  የሚያስነሳ ነው ብለዋል፡፡

መተግበሪያው ከተጠቃሚው መረጃ ለቻይና መንግስት ሊያስተላልፍ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩ ይታወቃል፡፡

እገዳው አስፈልጎ የነበረውም የአሜሪካ ዜጎች የግል መረጃን ቻይና ከምታደርገውን መረጃ መሰብሰብ ለመታደግ ነው ተብሏል፡፡

ዊቻት በአሜሪካ ብቻ 20 ሚሊየን ሚደርሱ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.