Fana: At a Speed of Life!

ፍቅረኛን ለማስደሰት በፈጸመው ድርጊት ለእስር የተዳረገው ወጣት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ፍቅረኛን ለማስደሰት በፈጸመው ድርጊት ለእስር የተዳረገው ወጣት፡፡ ከወደ ህንድ ሰሞኑን የተሰማው ዜና ብዙዎቹን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
በህንድ ኒውደሊህ ከተማ ኑሮውን ያደረገው ላሊት የተባለ ግለሰብ ከሰሞኑ ፍቅረኛውን ለማስደሰት ብሎም ለማስደመም የሞተር ብስክሌት የሰረቀ ሲሆን ይህም ለእስር ዳርጎታል፡
ለዚህም ያነሳሳው ፍቅረኛው አንድም የሞተር ሳይክል የለህም ብላ መሳለቋ ነበር ÷ በዚህ ልቡ የተነካው ግለሰቡ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን አንድ ዘዴ ዘይዷል፡፡
ዘዴውም በኒውደሊህ አሉ የተባሉ ዋጋቸው ውድ የሆኑ የሞተር ሳይክሎችን በመስረቅ እና የግሉ በማድረግ ፍቅረኛውን ማስደመም ነበር፡፡
ይህ ውጥናቸው ተሳክቶም ወደ ስምንት የሚጠጉ የሞተር ሳይክሎችን የሰረቁ ቢሆንም መጨረሻው እሱ እንዳሰበው ሳይሆን በተቃራኒው ራሱን እስር ቤት አግኝቷል፡፡
የሞተር ሳይክል ስርቆት ሪፖርት የቀረበለት የከተማዋ ፖሊስም ባደረገው ክትትል የሞተር ቀበኞቹን ላሊት እና ጓደኞቹ በቁጥጥር ስር አውሏል።
በመጨረሻም ፍቅረኛውን ለማስደሰት እና ለማስደመም በኒውደሊህ ተለያዩ ቦታዎች በመዟዟር ስምንት የሞተር ሳይክሎችን መስረቁን ለፖሊስ ተናግሯል፡፡
ይህ ድርጊቱም ለእስር እንደዳረገው ተሰምቷል፡፡
ምንጭ፡-ኦዲቲ ሴንተራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.