Fana: At a Speed of Life!

ፏን ኋን የሲሚንቶ ምርት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፏን ኋን የሲሚንቶ ምርት ጥቅም ላይ እንዳይውል መታገዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ፏን ኋን ሲሚንቶ የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ያላሟላ በመሆኑ፥ ማስተካከያ እስከሚያደርጉ ድረስ ከሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የብሔራዊ ደረጃ ምልክት እና ምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ሰርተፊኬት) የመጠቀም ፈቃድ የታገደ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ የብሔራዊ ደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ እና ምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይኖራቸው ሲሜንቶ ምርት በገበያ ላይ መገኘቱ እና ከምርቱ ጥራት ጋር ተያይዞ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በፋብሪካው በአካል በመገኘት ምርት ማምረትና እና አለማምረቱን ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያለው፡፡
በመሆኑም የብሔራዊ ደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ እና ምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ታግዶ እያለ÷ ጥራቱና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ ምርቶች በተጭበረበር መልኩ በማምረት የህብረተሰብ ደኅንነት እና ኢኮኖሚ የሚጎዳ ፏን ኋን ሲሚንቶ ወደ ገበያ ያሰራጨ በመሆኑ በድርጅቱ ላይ ቀጥለው ተጠቀሱት ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡
በራሱ ወጪ ፏን ኋን ሲሚንቶ ምርቱን ካሰራጨበት የሀገሪቱ የገበያ ቦታዎች ላይ እንዲሰበስብ እና ፏን ኋን ሲሚንቶ የምርት ጥራቱ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ ከመጠቀም እንዲቆጠብ ውሳኔ መተላለፉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.