Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታን አሜሪካ በዴሞክራሲ ላይ የምታዘጋጀውን ስብሰባ ላለመካፈል ወሰነች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓኪስታን አሜሪካ በበይነ መረብ በምታዘጋጀው የዴሞክራሲ መድረክ ላይ ላለመሳተፍ መወሰኗን ገለጸች፡፡

የፓኪስታን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ በዴሞክራሲ ላይ በምታካሂደው የበይነ መረብ ስብሰባ ላይ ሀገራቸው እንድትሳተፍ ስለተጋበዘች አመስግኗል፡፡

ፓኪስታን ነጻ የዳኝነት ሥርዓት፣ የነቃ ሲቪል ማኅበረሰብ እና ገለልተኛ መገናኛ ብዙኃን ያላት ዴሞክራሲያዊ ሀገር ናት፤ ዴሞክራሲን የበለጠ ለማጠናከር፣ ሙስናን ለማስወገድ እንዲሁም የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ለመጠበቅ እና ለማስከበር ቁርጠኛ ነች ብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፓኪስታን እነዚህን ግቦች ለማሳካት ሰፊ ማሻሻያዎች እያደረገች ትገኛለች ፤ የተወሰዱት የማሻሻያ እርምጃዎችም በሀገሪቷ ላይ አወንታዊ ለውጥ አምጥተዋል ሲልም ገልጿል፡፡

ከአሜሪካ ጋር ላለን መልካም ግንኙነት እውቅና እንሰጣለን፤ በቀጣይ በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብሮች ላይ ያለንን ግንኙነትም ማሻሻል እንፈልጋለን ነው ያለው፡፡

“በበርካታ ጉዳዮች ከአሜሪካ ጋር መልካም ግንኙነት አለን፤ በተጠራው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያለንን ምልከታም አግባብ መስሎ በታየን ጊዜ እንገልጻለን ብሏል፡፡

አሜሪካ በዴሞክራሲ ላይ የምታዘጋጀው የበይነ መረብ ስብሰባ የሚካሄደው ዛሬ እና ነገ ሲሆን፥ ቻይና እና ሩሲያ በስብሰባው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ አልቀረበላቸውም ነው የተባለው፡፡

ፓኪስታን ንግግሮችን እንዲሁም ለጋራ ተጠቃሚነት የሚካሄዱ ዓለም አቀፋዊ ትብብሮችን ለመደገፍ ገንቢ ሚና መጫወት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ቲ አር ቲ ወርልድ አመላክቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.