Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተመድ የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የትምህር ቅድመ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወቅር ዘውዴ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ በሚደረገው የትምህር ቅድመ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

በጉባኤው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የ154 አገራት የትምህርት ሚኒስትሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ትምህርት የዜጎችን ሁለንተናዊ አቅም የመለውጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ቅድመ-ጉባዔው የፊታችን መስከረም ወር በኒውዮርክ ለሚካሄደው የትምህርት ጉባኤ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድርግ ያለመ መሆኑን በፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.