Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በፈረንሳይ እየተከበረ በሚገኘው የጂቡቲ የነጻነት ቀን በዓል ላይ ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የጂቡቲ ኤምባሲ በፈረንሳይ እያከበረ በሚገኘው የጂቡቲ 45ኛ ዓመት የነጻነት ቀን በዓል ላይ ተገኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ያላቸውን የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት ምክንያት በማድረገ በሀገሪቱ የ45ኛ መት የነጸነት ቀን በዓል ላይ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተመድ የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ በሚደረገው እና በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው የትምህር ቅድመ ጉባኤ ላይ መሳተፋቸውን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.