Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከአፍሪካ ተጠቃሚነት ኮርፖሬሽን አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ከተቋቋመው የአፍሪካ ተጠቃሚነት ኮርፖሬሽን አባላት እና ከፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የሥራ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

በዚህ ወቅት የአፍሪካ ተጠቃሚነት ኮርፖሬሽን ከህብረት ሥራ ማህበራትም ሆነ ከአነስተኛ ገበሬዎች ጋር በመተባበር ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ በሚልኩበት መንገድ ላይ ያያዘው ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

እንዲሁም አርሶ አደሮች ለሚያመርቱት ምርት ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኙ ስለሚደረገው ጥረት ማብራርያ መስጠታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.