Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ ውይይቶችን አድርገዋል።

ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከርን በተመለከተ መክረዋል።

ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በነበራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት ግንኙነቶች እና በምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቅርቡ በሞት የተለዩትን የታንዛንያ ፕሬዝዳንት በመተካት ወደ ስልጣን ከመጡት ሳሚያ ሱሉሉ ሀሰን ጋርም ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ፕሬዘዳንቷ ሳሚያ ሀሰን ሱሉሉን በማንኛውም ነገር ለመርዳት ቃል ገብተዋል።

በተለይም በአፍሪካ ሴቶች ኔትወርክ በኩል በርካታ ድጋፍ እንደሚያገኙ እና እርሳቸውም ብዙ ድጋፍ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ  መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.