Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአየር ንብረት ለዉጥ  እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አደጋ መጨመር ላይ ያተኮረ ውይይት ላይ ተካፈሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአየር ንብረት ለዉጥ ያስከተለዉ ዘርፈ ብዙ ችግር ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አደጋ መጨመር ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት ላይ ተካፈሉ።

በውይይቱ ላይ ከ30 በላይ የሀገር መሪዎች፣ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ሃላፊዎችና ሚኒስትሮች የተገኙበት መሆኑ ተመላክቷል።

በዚሁ ወቅት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ንብረት ለዉጥን ያማከለ አሰራር ከመቅረጽ አኳያ እየወሰደ ያለዉን እርምጃ አንስተዋል።

የሁለቱ ትልልቅ ተግዳሮቶች መደራረብን ለመጋፈጥ ከአለም አቀፍ ትብብርና ቅንጅት ዉጪ ሌላ መላ እንደሌለዉ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝደንቷ በአፍሪካ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም በአፍሪካ ልማት ባንክና ግሎባል ሴንተር ኦን አዳፕቴሽን በተሰኘዉ ድርጅት እየተሰራ ያለዉን ትልቅ ስራ ማበረታታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.