Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጊኒ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በዓለ ሲመት ላይ ታደሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በዓለ ሲመት ላይ ተገኙ፡፡
ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ከ10 ዓመት በፊት በምርጫ የጊኒ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ ሀገሪቱን ለሁለት የምርጫ ዘመን በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።
በዘንድሮው ምርጫ ለሦስተኛ ጊዜ የተመረጡት ሃገሪቱ ያደረገችውን ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ተከትሎ ነው።
ቃለ መሀላ በፈጸሙበት ወቅትም ለሃገሪቱ ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲሁም ለአስተማማኝ ሰላም እና ፀጥታ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂያዊ አጋርነት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በመሪዎች ደረጃ በሁለቱም ሀገራት ጉብኝቶች ተደርገው፣ በጤና ፣ ግብርና፣ ቱሪዝም እና የተማረ የሰው ኃይል ለመለዋወጥ የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈርመዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት ዘመናቸው ካገልገሉባቸው ሀገራት መካከል መቀመጫውን ሴኔጋል ባደረገው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጊኒ ኮናክሬ ትገኝበታለች።
የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂያዊ አጋርነት እንዲቀየርም በርካታ ሥራዎች መስራታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንቷ ትናንት ማምሻውን ጊኒ ኮናክሪ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
59,904
People Reached
1,940
Engagements
Boost Post
1.1K
14 Comments
27 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.