Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በጅቡቱ የሚገኙ የሎጀስቲክ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጅቡቱ የሚገኙ የሎጀስቲክ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ።

በዚህ ወቅት ፕሬዚዳንቷ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወሳኝ የሆነውን የሎጀስቲክ መሰረተ ልማት አቅም ማሻሻል የሚቻልበትን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በትናትናው ዕለት ጅቡቲ የገቡት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  ከፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታውስ ነው።

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለትም በጅቡቲ ብሄራዊ ምክር ቤት በመገኘት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.