Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀረር ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሀረር ገባ፡፡
የልዑካን ቡድኑ ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሃመድ ቡህ አቀባበል አድርገውለታል።
ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ ሀረር የሚገኘው የፌስቱላ ሆስፒታል፣ ሸሪፍ ሙዚየምና ኢናይ አቢዳ የእደጥበብ ኮሌጅን እንደሚጎበኝ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም የማገገሚያ ማዕከል እንደሚመርቁና የሰብዕና ማዕከል የመሰረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ከሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.