Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለአዳዲስ አምባሳደሮች የሥራ መመሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን ወክለው ወደ ተለያዩ ሀገራት ለተመደቡ አዳዲስ አምባሳደሮች የሥራ መመሪያ ሰጡ፡፡

በተለያዩ ሃገራት የተመደቡ አምባሳደሮች በዛሬው እለት ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

በሽኝት ስነስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያና በተሾሙበት ሃገር መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንዲተጉ አሳስበዋል፡፡

ተሿሚ አምባሳደሮቹ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.