Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የአንድነት ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአንድነት ፓርክን ጎበኙ።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ፓርኩን ደጋግመው የጎበኙት ፕሬዚዳንቷ በዛሬው ጉብኝታቸው በየጊዜው አዳዲስ ነገሮች በፓርኩ እየተጨመሩ መምጣታቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ፓርኩን “አንድ ጊዜ አይቸዋለሁ ተብሎ የሚቀርበትና ታይቶ የሚጠገብም አይደለም” ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ በተለይ የኢትዮጵያውያንን ታሪክ ከማሳየትና ለትውልድ ከማስተላለፍ አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የአትዮጵያ ከተሞች ተመሳሳይ ዓይነት ታሪካዊ መዝናኛዎች እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመው፥ አንድነት ፓርክ የኢትዮጵያንም ሆነ የአዲስ አበባን መልካም ገፅታ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ነው ያመለከቱት።

ከፓርኩ በተጨማሪ ታላቁን ብሄራዊ ቤተ መንግስት ጨምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ ሊያሳዩ የሚችሉ ስራዎች በቀጣይ እንደሚከናወኑም በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።

ይህ ፓርክ ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቷ ኢትዮጵያ ብዙ የሚታዩ ታሪኮች እና ቅርሶች ባለቤት መሆኗን ማሳያ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ፓርኩን ሌሎች መጥተው እንዲመለከቱት በቅድሚያ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ፓርኩን ሊያውቁት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በፓርኩ ግንባታ ከመነሻ አሁን እስካለበት ደረጃ አሻራቸውን እያሳረፉ ላሉ ኢትዮጵያውያንን አመስግነዋል።

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.