Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቁልፍ የዶናልድ ትራምፕ ፖሊሲዎችን መከለስ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ ፖሊሲዎች ላይ ክለሳ ማድረግ ጀመሩ፡፡

ባይደን ቃለ መሃላ ፈጽመው ወደ ነጬ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ “የተደቀኑ ፈተናዎችን ለመፍታት የምናጠፋው ጊዜ የለም” ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በጀመሩት የክለሳ ስራም በዋናነት የፌደራል መንግስቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል ያሉትን 15 ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዞች ፈርመዋል፡፡

ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከስደተኞች ጋር በተያያዘ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ይከተሏቸው የነበሩ ፖሊሲዎችን የሚሽሩ ትዕዛዞችንም በባይደን ተፈርመዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሃገራቸውን ዳግም ወደ 2015ቱ የፓሪስ ስምምነት ለማስገባት የሚያስችላትን ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ በፊርማቸው አኑረዋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በትራምፕ አስተዳደር ተይዞ ከነበረው አቋም የተለየና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያግዝ አዲስ አካሄድ ይከተላሉም ተብሏል፡፡

ይህን የሚያግዝ አዲስ ቢሮ የሚቋቋም ሲሆን፥ አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት ለመውጣት የጀመረው ሂደትም ይቋረጣል ነው የተባለው፡፡

አሜሪካውያንም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታን መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

ባይደን ዶናልድ ትራምፕ በአንዳንድ የሙስሊም ሀገራት ላይ ጥለውት የነበረውን እገዳም አስነስተዋል ነው የተተባለው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.