Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፈሰር ጥሩሰው ተፈራ የጆርጅ ፎስተር የምርምር ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የስነልቦና እና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮፌሰር የሆኑት ጥሩሰው ተፈራ በሀምቦልት ፋውንዴሽን የጆርጅ ፎስተር የምርምር ሽልማትን አገኙ።

ፋውንዴሽኑ በድረገፁ ባወጠው መረጃ ፕሮፈሰር ጥሩሰው ተፈራ በልዩ ፍላጎት ትምህርት ዘርፍ ለሀገራቸው ብሎም ለአፍሪካ ያበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሽልማቱ እንዳበቃቸው አመልክቷል።

ፕሮፈሰር ጥሩሰው ተፈራ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ባላቸው ፍላጎት፣ በሚያስፈልጓቸው ክብካቤዎች እና ተሃድሶ ዙሪያ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን አካሂደዋል።

በአጠቃላይ በዘርፉ ያደረጓቸው ጥናቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርት በሀገሪቱ እንደ አንድ የሳይንስ ትምህርት ዘርፍ በትምህርት  ስርዓት ውስጥ እንዲካተት ምክንያት መሆናቸውንም ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.