Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የጂኦግራፊ መምህር፣ ፖለቲከኛ፣ ደራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም በፕሮፌሰር መስፍን እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫቸው “የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል” ብለዋል።

“ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ” ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.