Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ከ1950 አስከ 1960ዎቹ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ በሴማዊ ቋንቋ ጥናት፣ በአማርኛ ግዕዝ ሥነ-ጹሑፍ እና ሰዋሰው በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በአማርኛ ቋንቋ ከታተሙ ሥራዎቻቸው መካከል ደቂቀ አስጢፋኖስ፣ አንዳፍታ ላውጋችሁ፣ ስለግዕዝ ሥነ-ጹሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ባሕረ ሐሳብ የሚሉት እንደሚገኙበት ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በሀገራዊ ጉዳዮች በሚሰጡትም በሳል ሀሳቦች እና ትችቶችም በሕዝብ ዘንድ ይታወቃሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.