Fana: At a Speed of Life!

ፖለቲከኞች ከአድዋ ድል ሊማሩ ይገባል –  የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖለቲከኞች ከታላቁን የአድዋ ድል በርካታ ቁም ነገሮችን ሊማሩ እንደሚገባ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች ተናገሩ ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉትና በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ይሄነዉ ምስራቅ፣ ፖለቲከኞች ከድሉ የአላማ ጽናትን መማር ይገባቸዋል ብለዋል።

ፖለቲከኞች ድሉን ከመዘከር ባለፈ ለሃገራዊ አላማ ጽናት ወሳኝ መሆኑን ተረድተው ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል።

ሌላኛዉ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና ተመራማሪ ሱራፌል ጌታሁን ፣ ድሉ ስለ ሃገር ሉአላዊነት እና ነጻነት የተከፈለ ዋጋ እንደመሆኑ ወቅታዊው የሃገሪቱ ፖለቲካ ከዚህ ታላቅ ገድል ሊማር እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

ምሁራኑ የድሉ ባለቤቶች በወቅቱ ልዩነት ቢኖራቸውም ስለ ሃገር አንድነት የተደረገ ጥሪ እንዳሰባሰባቸው አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ መደማመጥ እና በሃሳብ ልእልና የማመን ሁነት ደግሞ የአሁኑ ፖለቲከኞች ሊማሯቸው የሚገቡ አንኳር ጉዳዮች እንደሚበዙም አስረድተዋል።

ወርቃማውን የአድዋ ድል ፖለቲከኞች በአስተውሎት መመልከት ከቻሉ፣ ከሴራ እና የመፈራረጅ ፖለቲካ ወጥተው ስለ ህዝብ እና ስለ ሃገር አርቀው እንዲያስቡ የሚያግዝ ስለመሆኑም ተናግረዋል ።

አድዋ ታላቅ ሃሳብ መሆኑን የሚያስረዱት ምሁራኑ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች እሳቤያቸውን በሃገራዊ እሴት እና ብዝሃ ማንነትን ባከበረ መልኩ እንዲቃኙ ያግዛልም ብለዋል።

ስለ ጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ ብሩህ ተስፋ እንዲሁም ተቀራርቦ ስለ መነጋገር  ከታላቁ የአድዋ ድል ትምህርት መውሰድ እንደሚቻልም ገልጸዋል፡፡

 

በአወል አበራ መኮንን

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.