Fana: At a Speed of Life!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ60 መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነትና የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ60 የዩኒቨርሲቲው መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነትና የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የማዕረግ ዕድገቱን ያገኙት የዩኒቨርሲቲው መምህራን በተለያዩ ካምፓሶችና ትምህርት ክፍሎች  የሚያገለግሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መምህራኑ ከወራት በፊት በየኮሌጆቹ (በየፈካልቲው) ታይቶና ተወስኖ የቀረበውን የታሪከ ማህደራቸውን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት መርምሮ ለዕድገቱ የተቀመጡ መመሪያዎችንና መስፈርቶችን አሟልተው መገኘታቸውን ካረጋገጠ በኋላ እድገቱን ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

ወደ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያደጉ መምህራን 18 ሲሆኑ የተቀሩት 42ቱ ደግሞ ወደ ረዳት ፕሮፌሰርነት ያደጉ መምህራን መሆናቸውን የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት መረጃ ያመለክታል፡፡

እንዲህ ዓይነቱን የማዕረግ የደረጃ ዕድገት ሲሰጥ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው  ከዚህም ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በየእርከኑ  የማዕረግ እድገቶች ሲሰጥ መቆየቱን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.