Fana: At a Speed of Life!

ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ።

ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር የተለያየው ሀዲያ ሆሳዕና የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያን በምትካቸው ሾሟል።

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ዛሬ በክለቡ ጽህፈት ቤት በመገኘት እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የሚያቆያቸውን የኮንትራት ፊርማ አኑረዋል።

በቀሪዎቹ የሊጉ ጨዋታዎችም ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ክለቡን በሊጉ ለማቆየት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ክለቡ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወሳል።

ዘንድሮ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ሀዲያ ሆሳዕና ካደረጋቸው 12 ጨዋታዎች በ7ቱ ተሸንፎ በ9 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከክለቡ የፌስ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.