Fana: At a Speed of Life!

ሀገራት ተገቢውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች እየተገበሩ አይደለም- ዶ/ር ቴድሮስ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገራት ተገቢውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች እየተገበሩ አለመሆኑን የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።

የተለያዩ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ጥከለዋቸው የነበሩ ክልከላዎችን እያቀለሉ እና በሂደት እያነሱ ይገኛሉ።

ይህንን ተከትሎም የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እያገረሸ መምጣቱን የሚወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ትናንት በሰጡት መግለጫም፥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ይረዳሉ በሚል የተቀመጡ መመሪያዎችን ሀገራት በተገቢው መንገድ እየተገበሩት አይደለም ብለዋል።

በዚህም የተነሳ የቫይረሱ ስርጭት በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑንም ዶክተር ቴድሮስ በመግለጫቸው አንስተዋል።

የኮሮና ቫይረስ ለመግታት ይረዳሉ በሚል የተቀመጡ መመሪያዎች በተገቢው መንገድ ካልተተገበሩም የቫይረሱን ስርጭት በአጭር ጊዜ መግታት ይቻላል ብሎ ማሰብ ከባድ ሆኗልም ብለዋል።

አሁንም የወጡ የቫይርሱ ስርጭት መግቻ መመሪያዎች ሳይሸራረፉ  እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.