Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የንቅናቄና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልል ደረጃ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የንቅናቄና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልል ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ እስከ ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፥ በየደረጃዉ የሚገኙ የስፖርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል።

በሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያው ላይ በአዳማ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ የሆኑበት ውይይት ትናንት ተካሂዷል።

ይህ ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የውይይት መድረክ ዛሬ በጋምቤላና ባህር ዳር እየተካሄደ ሲሆን፥ በዚህ መድረክ ላይ ከወረዳ እስከ ፌደራል የሚገኙ ባላድርሻ እና ሌሎች አጋር አካላት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ነገ ደግሞ በአሶሳ እና በድሬዳዋ ከተሞች የሚካሄድ ሲሆን በቀጣይ በሐረርና ጅግጅጋ ከተሞች እንደሚካሄድ ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.