Fana: At a Speed of Life!

ሀገርን በፀና መሰረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአባቶችን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ሃላፊነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በይፋ አብስረዋል።
በዚህ ወቅትም “ይህ ትውልድ አባቶቻችን ያሰቡትን ህልም እና ፍላጎት እውን በማድረግ ሀገርን በፀና መሰረት ላይ የማቆም ሃላፊነት እንዳለበት ሊገነዘብ ይገባል” እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በታሪክ ውስጥ ማለፍ እና ታሪክ መስራት ይለያያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “በታሪክ ውስጥ ማለፍ እድል፤ ታሪክ መስራት ደግሞ ድል ነው” ብለዋል ።
በታሪክ ውስጥ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ታሪክ መስራት ግን በመገኘት እውቀትን፣ ገንዘብን፣ ሃሳብን፣ ጉልበትን በመስጠት አንድ ሁነት እንዲከወን ማድረግ ከዕድል ያለፈ ድል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የዚህ ድል እና እድል ባለቤት ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የህዳሴው ግድብ አባቶች አስበውት፣ አቅደውትና ተመኝተውት ዛሬ ዕውን መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ግድቡ ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ ያዩ የዛሬው ትውልድ አባላት እድለኞች መሆናቸውንም አውስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን እና ውድ ህይወታቸውን የከፈሉበት ፕሮጄክት መሆኑም አንስተዋል።
ዜጎችም ዛሬ የፕሮጄክቱን እዚህ መድረስ በዕድልና በድል መመልከታቸውን አቅልለው ባለማየት ለላቀ ድል መነሳት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የህዳሴ ግድብ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ በስፍራው በተለያየ መልኩ አገልግሎት ለሚሰጡ የግድቡ ሰራተኞችን ጨምሮ በተለያየ መልኩ ድጋፍና እገዛ ላደረጉ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
634
People reached
7,249
Engagements

-1.2x average

Distribution score
Boost post
Hussen salih ሁሴን ሳሊህ and 3.2K others
229 Comments
260 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.