Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም ዕሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው –  ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም ዕሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋ ለመፍጠር ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም ዕሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት ትምህርት ሚኒስቴር አውደ ጥናት እያካሄደ  ነው።

አውደ ጥናቱ በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ የሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ ዜግነትና የሰላም ዕሴቶች ላይ ግብዓት መሰብሰብ ዓላማ  ያደረገ ነው ተብሏል።

የሚሻሻለው የግብረ-ገብና ዜግነት ትምህርት ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የግብረ-ገብ ትምህርት እንዲሁም ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ደግሞ የዜግነት ትምህርት ተብሎ እንደሚዘጋጅ ይጠበቃል፡፡

ለሚዘጋጀው  የግብረ-ገብና ዜግነት ትምህርት  ስርዓተ ትምህርት  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከወሎ ዩኒቨርስቲ፣ ከአዲስ ኪነ-ጥበባት የባህል ማዕከል፣ ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔና ከሌሎች ተቋማት የመጡ ከፍተኛ ምሁራን፣ተመራማሪዎች፣ የፍልስፍናና  የሀይማኖት ሰዎች  ጥናታዊ ፅሁፎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመድረኩም ከክልል ትምህርት ቢሮ፣ ከመምህራን ማህበር፣ ከመምህራን ኮሌጆች፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድረሻ አካላት የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ማሰተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከስርዓተ-ትምህርቱ ችግሮች መካከል የግብረ-ገብ ትምህርትን በሚፈለገው ልክ አካቶ አለመያዙ መሰረታዊ ችግር ሆኖ በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታው ላይ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.