Fana: At a Speed of Life!

ሀገር የከዱ የሠራዊት አባላትን በወታደራዊ ሕግ መዳኘት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለሕግ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ዳይሬክቶሬት ከጁንታው ጋር በማበር ሀገር የከዱ የሠራዊት አባላትን ፍርድ ለመስጠት በሚያስችሉ ሕጎች ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡

የመከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል ደምሴ ካሳ፥ ከሁሉም ዕዝና አየር ኃይል ለተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎች ፣ ከፅንፈኛው ሕወሓት ጋር ተሰልፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ አባላትን በወታደራዊ ሕግ ለመዳኘት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።

የሥልጠናው ተካፋዮችም አዳዲስ ተፈፃሚ በሚሆኑ ሕጎችና አሠራሮች ላይ ጥሩ ግንዛቤ መፍጠር መቻላቸውን ተናግረዋል።

የመከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ዳይሬክቶሬት ሀገር የከዱና የጁንታውን ተልዕኮ በማስፈጸም የተጠረጠሩ አባላትን በወታደራዊ ሕግ የመዳኘት ሥራውን በቅርቡ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.