Fana: At a Speed of Life!

ሀገር የካደውን የህወሃት የጥፋት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ በአምቦ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሃት የጥፋት ቡድን የፈፀመውን ክህደት የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ በአምቦ ከተማ ተካሄደ።
የአምቦና የአካባቢዋ ነዋሪዎች እያካሄዱ ባሉት ሰልፍ አረመኔው የጥፋት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ጠላት መሆኑን በመግለጽ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል።
መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።
በከሃዲው የህወሃት ቡድን ሴራ አንድነታችን አይናጋም፣ ከጀግናው መከለከያ ሠራዊታችን ጎን እንቆማለን፣ አንድነታችንን አጠናክረን የህወሃትና የተላላኪዎቹን አፍራሽ ተልእኮን እናጋልጣለን፣ አጥፊው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የሀገር ክህደት እኩይ ተግባር እናወግዛለን፤ የሚሉ መፈክሮችን ማሰማታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.