Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን እየተካሄደ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን በዛሬው እለት በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዕለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ራሳችንን ከኮሮና ወረርሽኝ እየጠበቅን አረንጓዴ አሻራችንን እናኑር ብለዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ በአራት ዓመታት 20 ቢሊየን ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም እየሠራች መሆኑን ተናግረዋል።

በዘንድሮው መርሃግብርም 5 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል መታቀዱንም ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት ከተተከሉት የአረንጓዴ አሻራ ችግኞች መካከል 84 ከመቶ መጽደቃቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዘንድሮው መርሀ ግብር የፌደራልና የክልል መንግሥታት በጋራ በመሆን እቅዱን ለማሳካት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተያያዘም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እያከናወኑ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.