Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨቱ ግድቡን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሻግረዋል – ቲቦር ናዥ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ግድቡን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሻጋግረዋል ሲሉ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ናዥ ተናገሩ።

ግብጽ በዚህ ዙሪያ መግለጫ ልታወጣ እንደምትችል የገለጹት አምባሳደሩ፥ ነገር ግን ጉዳዩን የሚወስኑት በመሬት ላይ ያሉ እውነታዎች መሆናቸውን በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በመሆኑም በግብጽ በኩል ከስሜታዊነት ይልቅ ባሉ እውነታዎች ላይ ተመስርቶ መደራደር የሚሻል መሆኑንም ቲቦር ናዥ መክረዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.