Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም ወገን ለሃገር እና ለወገን ቅድሚያ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁሉም ወገን ለሃገር እና ለወገን ቅድሚያ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳስቧል።
 
ጉባዔው ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፤
ጉባዔው በመግለጫው አስቀድሞ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ወገኖች ላይ በተፈጸመው የግፍ ግድያ የተሰማዉን ሃዘን ገልጿል።
 
በፌዴራል መንግስት እና ህወሃት ውስጥ ካሉ ቡድኖች መካከል የተፈጠረው ግጭት እንዳይባባስ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት፤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚያስተላልፉትን መልዕክት ችግሩን ከማባባስ የተቆጠበ እና በአንፃሩ ለሰላም ጥሪ የሚያደርግ እንዲሆን ሲል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔዉ አሳስቧል።
 
በሀገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን የጥላቻ እና የክፋት መንፈስ እንዲወገድ ሁሉም እንደየ እምነቱ ስርዓቱ ፤ወደ ፈጣሪዉ በመመለስ ከነገ ጥቅምት 26 ጀምሮ ለ1 ሳምንት የሚቆይ የጸሎት እና የምህላ ጊዜ እንዲሆን ጉባዔው መግለጫው አስታዉቋል።
 
ይህን ተቀብሎም ሁሉም በጸሎት እንዲተጋ ጉቧዔው ጥሪ አቅርቧል።
 
በፍሬህይወት ሰፊው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.