Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ በብሪታኒያ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ የተሰኘው ግዙፍ የቻይና ቴሌኮም ኩባንያ በብሪታኒያ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል።

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሀገራቸው ከሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በቅንጅት ለመስራት ፍላጎት ያላት መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ መሰረትም ኩባንያው በቀጣይ በብሪታኒያ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት።

ሁዋዌ ቻይና ከአሜሪካ ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት እንዳይሰጥ ክልከላ የተደረገበት መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህ ባለፈም ኩባንያው አገልግሎት በሚሰጥባቸው ሀገራት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ይገባል በሚል ካናዳ እና አውስትራሊያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል።

ብሪታኒያ ከኩባንያው ጋር በቅንጀት ለመስራት እና አገልግሎቱን ለመጠቀም መፈለጓም ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ሊያሻክረው እንደሚችል ተሰግቷል።

ምንጭ፦ሲ ጂ ቲኤ ን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.