Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ በፈረንጆቹ 2019 240 ሚሊየን ስልኮችን ለገበያ አቅርቧል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም  ኩባንያ ሁዋዌ በፈረንጆቹ 2019 240 ሚሊየን ስልኮችን ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎም ኩባንያው የሽያጭ ገቢው 850 ቢሊየን ዩዋን ወይም 122 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል ፡፡

ሽያጩ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ 18 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፥ የተጠበቀውን ያክል ገቢ አለመገኘቱም ተመላክቷል ፡፡

የኩባንያው  መሳሪያዎቹን በመጠቀም ስለላ ሊያካሂድ ይችላል በሚል በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ባለሥልጣናት  ላይ ስጋትን በመጫሩ ከአሜሪካ የግንኙነት መረቦች በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዛዝ መታገዱ ይታወሳል ፡፡

ይህም ለሁዋዌ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሮ  ቆይቷል፡፡

ኩባንያው በ2020ም የተፈጠረውን ችግር በመቋቋም ገበያው ላይ መቆየት ተቀዳሚ አላማው መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል።

ምንጭ፡-www.cnet.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.