Fana: At a Speed of Life!

ሃገራችን ከወራሪ ለመጠበቅ ወደ ውትድርና ስልጠና ገብተናል – የጎንደር ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት ለመጠበቅ ወደ ውትድርና ስልጠና መግባታቸውን የጎንደር ከተማ ምልምል ወጣቶች ገለፁ።

ወጣቶቹ ይህን ያሉት በጎንደር ከተማ ወደ ስልጠና ለመሄድ ሽኝት በተደረገላቸው ወቅት ነው።

ምልምል ወጣቶቹ የኢትዮጵያን ጠላቶች ለመመከትና አሸባሪውን የህውሓት ሀይል ለመደምሰስ ወደ መከላከያ ሰራዊት መቀላቀላቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

በዞብል ክፍለከተማ 165 ወጣቶች መስፈርቱን አሟልተው መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ለመውሰድ መመልመላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ ተሳትፎ አደረጃጀት አማካሪ አቶ አዝመራው ተዘራ ተናግረዋል።

አማካሪው በከተማ ደረጃ 2ሺህ ወጣቶችን በመልመል የመከላከያ ሰራዊት አባል ለማድረግ የታቀደ ቢሆንም በቀናት ውስጥ ከ1ሺህ በላይ ወጣቶች የመከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን ወስነዋል ነው ያሉት።

በቀጣይም የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ለማጠናከር በከተማ ደረጃ ምልምል ወጣቶችን የመለየት ስራ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል ብለዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.