Fana: At a Speed of Life!

ሃገር በቀሉ ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ ለአውሮፓ ማይክሮ ፋይናንስ ሽልማት የመጨረሻ እጩ ዝርዝር ውስጥ ገባ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገር በቀሉ ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ የአውሮፓ ማይክሮ ፋይናንስ በሚያዘጋጀው አመታዊው የምርጥ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የመጨረሻዎቹ ዝርዝር ውስጥ ገባ፡፡

ተቋሙ በአውሮፓ ማይክሮ ፋይናንስ በተዘጋጀውና በፈረንጆቹ 2020 የምርጥ ማይክሮ ፋይናንስ ሽልማት የመጨረሻ ሶስት እጩዎች ውስጥ ተካቷል፡፡

ሽልማቱ ውጤታማና አካታች ቁጠባን ማበረታታት በሚል ዘርፍ የተዘጋጀ ሲሆን፥ የኔፓሉ ሙክቲናዝ ቢካስ ባንክ እንዲሁም የቤኒኑ ማይክሮ ፋይናንሰ ተቋም ከኢትዮጵያው ተቋም በተጨማሪ በመጨረሻዎቹ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡

በዚህ ሽልማት አሸናፊ የሚሆን ተቋም 118 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሽልማት የሚበረከትለት ይሆናል፡፡

ሶስቱ ተቋማት ለደንበኞቻቸው ተደራሽ በመሆን፣ አዋጭ ቁጠባን በመባረታታትና በመተግበር እንዲሁም የደንበኞቻቸውን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በሰሩት ስራ ተመራጭ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.