Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ በሀሰት ከሚሰራጩ አፍራሽ ተልዕኮዎች እንዲጠነቀቅ የአማራ ክልል መንግሥት አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ህብረተሰቡ በሀሰት ከሚሰራጩ አፍራሽ ተልዕኮዎች እንዲጠነቀቅ አሳሰበ፡፡
የአማራ ሕዝብ በከፈለው ወደር የለሽ ተጋድሎ ያስመዘገበውን ድል በመቀልበስ ለጠላቶቹ አሳልፈው በመስጠት ለዳግም ባርነት ሊዳርጉት የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች ሲሰሩ መቆየታቸው ተመላክቷል፡፡
አማራን ለማዋረድ ተቀናጅተው እየሰሩ የሚገኙ እነዚህ ኃይሎች በተለያየ ጊዜ የውሸት ሰነዶችን እያዘጋጁ ሲያሰራጩ መቆየታቸው የተገለጸ ሲሆን÷ ዛሬም እንደትናንቱ መንግስት እውቅና የሰጣቸውን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ጀግኖች የሆኑትን የአማራ ፋኖዎች እርምጃ ሊወስድ መሆኑን የሚገልጽ “የኦፕሬሽናል አፈጻጸም ዝርዝር ግዳጅ” የሚል የዳቦ ስም የሰጡት የበሬ ወለደ የፈጠራ ሰነድ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡
የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ኢትዮጵያን እንደ አገር ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ እንደማይችል የተረዳው አሸባሪው ትህነግና ወኪሎቹ እያሰራጩት ያለው የፈጠራ ሰነድ የአማራ ክልል መንግስት የማያውቀው በመሆኑ÷ ጠላት በቀጣይነትም በፈጠራ እና ውሸት የተሞሉ ሰነዶችን እያዘጋጀ ማሰራጨቱን መቀጠሉ አይቀሬ በመሆኑ መላው ሰላም ወዳድ የሆነው የክልላችን ሕዝብ ከመሰል የፈጠራ ሰነዶች እራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የሕዝባችን ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነውን የሰላም እና ደህንነት ጥያቄ ለመመለስ ምልዓተ ሕዝባችንን በማሳተፍ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ እርምጃ እየተወሰደ ሲሆን÷ በዚህ እርምጃም አንጸባራቂ ድል ተገኝቷል ብሏል፡፡
የሕዝባችን ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነውን የሰላም እና ደህንነት ጥያቄ ለመመለስ ምልዓተ ሕዝባችንን በማሳተፍ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ እርምጃ እየተወሰደ ሲሆን÷ በዚህ እርምጃም አንጸባራቂ ድል ተገኝቷል ተብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.