Fana: At a Speed of Life!

ህንድ የስልክ ጥሪ ድምጽን በኮሮና ቫይረስ መረጃ ተካች

አዲስ አበባ፣መጋቢት 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ ሞባይል ጥሪ በጤና መረጃ ተተክቷል፡፡

በሃገሪቱ እያንዳንዱ የስልክ ጥሪ ከመጀመሩ በፊት ለ30 ሰከንድ ስለኮሮና ቫይረስ የተለያዩ መረጃዎችን በመስጠት ላይ ነው ተብሏል፡፡

መልዕክቱ በእንግሊዝኛ የሚጀምር ሲሆን፥ በጥሪ ድምጽ ምትክ የሚያስል ሰው ድምጽ እንደሚሰማ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ስለ ቫይረሱ ምንነት እና ምልክቶች የተለያዩ መረጃዎች እንደሚሠጡ ነው የተነገረው፡፡

ይህም ሰዎች ስለ ምልክቶቹ በበለጠ እንዲረዱ እና እነሱም በቫይረሱ ከተያዙ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግንዛቤ እንዲጨብጡ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

በፈረንጆቹ ከመጋቢት 9 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ድምጽን በጤና መረጃ የመተካት ሂደት ብዙ የሚዲያ ሽፋን ባያገኝም ቫይረሱን በተመለከተ በርካታ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረጉ ተመላክቷል።

ይሁን እንጅ አንዳንድ ደንበኞች በድምጽ ጥሪው  ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎ በርካታ ድረ ገጾች የድምጹን ጥሪ ማስወገድ የሚያስችል መንገድ እየፈጠሩ መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚህም የተለያዩ ድረ ገጾች አንድ ቁጥርን ወይም ሃሽታግ ቁልፍን በመጫን እየደወሉ ድምጹን ማገድ መጀመራቸው ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.